am_tn/jer/25/37.md

1.6 KiB

ስለዚህ ሰላማዊዎቹ መሰማሪያዎች ይደመሰሳሉ

ያህዌ ለእስራኤል መሪዎች እረኞች እንደሆኑ አድርጎ መናገሩን ይቀጥላል፡፡ እዚህ ስፍራ አገሪቱ እነርሱ በሰላም እየኖሩባት እንደሆነ የሚያስቧት "መሰማሪያ" እንደሆነች ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላማዊዎቹ መሰማሪያዎች ከያህዌ ታላቅ ቁጣ የተነሳ ይደመሰሳሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከእርሱ ታላቅ ቁጣ የተነሳ ያህዌ ሰላማዊዎቹን መሰማሪያዎች ይደመስሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ እንደ ደቦል አንበሳ፣ ከዋሻው ወጥቷል

ያህዌ ህዝቡን በከፍተኛ ቁጣ መቅጣቱ የተገለጸው፣ ያህዌ አደን ለማደን ከዋሻው እንደወጣ አንበሳ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምድራቸው ማስደንገጫ/ማስፈራሪያ ይሆናል

"አስፈሪ/አሰቃቂ" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ምድራቸው ሰዎችን የሚያስፈራ ስፍራ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የጨቋኖች ቁጣ

ይህ የእስራኤልን ጠላቶች ቁጣ ያመለክታል፡፡