am_tn/jer/25/24.md

1.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ ምንባብ የያህዌን እጀግ ከፍ ያለ ቁጣ፣ የአገራቱ ህዝቦች ከጽዋው እንዲጠጡ እንዳደረጋቸው በዘይቤ መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዘምሪ

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ከወንድሙ ጋር

ይህ ከአንዱ በመቀጠል ሌላው እያንዳንዱ ሰው የሚል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ከአንዱ በመቀጠል ሌላው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም ጽዋውን ከያህዌ እጅ መጠጣት አለባቸው

እዚህ "ጽዋው" በውስጡ ለያዘው ወይን ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ/ ነው፡፡ "እነዚህ ሁሉ ሰዎች በያህዌ እጅ ካለው ጽዋ መጠጣት አለባቸው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)