am_tn/jer/25/05.md

2.4 KiB

እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱ እና ከብልሹ ምልልሱ ይመለስ

ኤርምያስ ሰዎች ይፈጽሙት የነበሩትን ድርጊት ስላቆሙ ሰዎች የሚናገረው እነዚያ ሰዎች ከዚያ ድርጊት ዞረው እንደተመለሱ አድርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ መንገዱ እና የልምምዶቹ ብልሽት

"ክፉ መንገድ" እና "የልምምዶቹ ብልሽቶች" የሚሉት አገላለጾች ተመሳሳ ትርጉም ሲኖራቸው የሚያደረጓቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ያመለክታሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የልምምዶቹ ብልሹነቶች

"ብልሹ ድርጊቶቹ"

ሌሎች አማልዕክትን አትከተሉ

ኤርምያስ ራሱን ለጣኦት አሳላፎ የሰጠን ሰው የሚገልጸው ያሰው ያንን ጣኦት ተከትሎ እንደሄደ አድርጎ ነው፡፡ "ራሳችሁን ለሌሎች አማልዕክት አሳልፋችሁ አትስጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእጆቻችሁ ስራ እርሱን አታስቆጡት/አታነሳሱት

"እርሱን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ "የእጆቻችሁ ስራ" የሚለው ሀረግ ሊሰጠው የሚችሉት ትርጉሞች 1) ይህ የሚያመለክተው ሰዎች በእጆቻቸው የሚሰሯቸውን ጣኦታት ነው፡፡ "ያህዌን በሰራችሁት ጣኦት አታስቆጡት/አታነሳሱት" ወይም 2) "እጆች" ከሚለው ቃል ጋር እነዚያን ድርጊቶችን የሚወክል ሴኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/በመሆን የአንድን ሰው ድርጊት የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ "በምታደርጓቸው ነገሮች ያህዌን አታስቆጡት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ እንዲሁም ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)