am_tn/jer/23/33.md

3.1 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ያህዌ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን እና በኤርምያስ 23፡40 ላይ የሚጨርሰውን መልዕክቱን ማድረሱን ይቀጥላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 33-40 ድረስ "ሸክም" የሚለውን ቃል በመደጋገም የሚደረግ አገላለጽ አለ፡፡ አንዳንዴ "መልዕክተኛ" ማለት ሲሆን በሌላ ጊዜ "ለመሸከም ከባድ የሆነ ሸክም" ማለት ይሆናል፡፡ ከተቻለ ይህ የቃላት ድግግም አገላለጽ እንዳለ ሊጠበቅ ይገባዋል፡፡

አንተን እጠይቅሃለሁ… አንተ እንዲህ ትላለህ

በእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች "አንተ" የሚሉት ነጠላ ቁጥር ሲሆኑ ኤርምያስን ያመለክታሉ፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

የያህዌ ሸክም ምንድን ነው?

እዚህ ስፍራ "ሸክም" ማለት ከያህዌ ዘንድ የሆነ መልዕክት ወይም ትንቢት ማለት ነው፡፡

ሸክሙ እናንተ ናችሁ… እናንተን አስወግዳለሁ

እነዚህ "እናንተ" የሚሉት ሁለት ሁኔታዎች ብዙ ቁጥር ሲሆኑ የሚያመለክቱት ሀሰተኛ ነቢያትን እና ካህናትን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

ሸክሙ እናንተ ናችሁ

እዚህ ስፍራ "ሸክም" ማለት ከባድ ሸክም ነው፡፡ ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ እነርሱ ያህዌን ያስቆጣሉ እርሱም ከእንግዲህ ከእነርሱ ጋር መሆን አይፈቅድም ማለት ነው፡፡ "እኔ እናንተን በመሸከም ያደከማችሁኝ ሸክሞች ናችሁ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የያህዌ ሸክም ነው

እዚህ ስፍራ "ሸክም" ከያህዌ ዘንድ የሆነ መልዕክት ወይም ትንቢት ነው፡፡

የእርሱ ቤት/ቤቱ

እዚህ ስፍራ "ቤት" በውስጡ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "የእርሱ ቤተሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)