am_tn/jer/23/25.md

3.5 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ያህዌ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን እና በኤርምያስ 23፡40 ላይ የሚጨርሰውን መልዕክቱን ማድረሱን ይቀጥላል፡፡

በሀሰት ይተነብያሉ

"ማታለል" የሚለው ቃል በገላጭ ወይም ተውሳከ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የሚያታልሉ/ሀሰተኛ ነገሮችን እየተነበዩ" ወይም "በሀሰት/በማታለል እየተነበዩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ስም/በስሜ

ይህ ሀረግ የሚያመለክተው በያህዌ ሀይል እና ስልጣን ወይም እንደ እርሱ ተወካይ መናገርን ነው፡፡ ይህ ሀረግ በኤርምያስ 14፡14 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ህልም አለኝ!

ይህ ህልም ከእግዚአብሔር ነው ማለታቸው ነው፡፡ ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ከያህዌ ዘንድ የሆነ/የመጣ ህልም አለኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከራሳቸው አይምሮ ሀሰትን የሚተነብዩ ነቢያት፣ እና በልባቸው ውስጥ ካለው ሽንገላ የሚተነብዩ ነቢያት ትንቢት እስከ መቼ ይቀጥላል?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ነቢያቱ ይህንን ማድረጋቸውን መቀጠል እንደሌለባቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡"ነቢያት ራሳቸው ያበጇቸውን ሀሰተቶች ማወጃቸው መቀጠል የለበትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከራሳቸው አይምሮ የሆነ የሀሰት ትንቢት… በልቦቻቸው ካለ ሽንገላ የሆነ ትንቢት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ሀሰተኛ ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ራሳቸው እንደሚያበጇቸው ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "ከራሳቸው አይምሮ ብቻ የሚመነጩ ትንቢታዊ ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ስሜን ረሱ… ስሜን ረስተዋል

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚለው ቃል በአጠቃላይ የያህዌን ማንነት ያመለክታል፡፡ "ህዝቤ እኔን ከማምለክ ይልቅ በኣልን እንደሚያመልክ አድርገዋል/መርተውታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የበኣልን ስም በመምረጥ

እዚህ ስፍራ "የበኣል ስም" የሚያመለክተው በኣል የተባለውን ጣኦት ነው፡፡ "ህዝቤ እኔን ከማምለክ ይልቅ በኣልን እንዲያመልክ መርተውታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)