am_tn/jer/23/19.md

2.2 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤርምያስ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን የያህዌ መልዕክት ማድረሱን ይቀጥላል፡፡

ይህ ከያህዌ ዘንድ የመጣ መዕበል ነው…ቁጣው እየወጣ ነው… አውሎ ነፋስ በሃይል እየተሸከረከረ እየነፈሰ ነው

እነዚህ ሶስት ሀረጎች ሁሉም ታላቅ ማዕበልን ሲገልጹ ይህም የያህዌን ቁጣ የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በተነጻታሪ ዘይቤ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የያህዌ ቁጣ እንደ ታላቅ ማዕበል፣ በቁጣ ወጥቶ እንደ አውሎ ነፋስ በሀይል እየተሽከረከረ እየመጣ ነው" (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አውሎ ነፋስ

ሀይለኛ የነፋስ ማዕበል

በክፉዎች ራስ ላይ በሃይል እየተሽከረከረ የነፍሳል

የያህዌ ቁጣ የተነገረው በክፉዎች ዙሪያ እንደሚነፍስ አውሎነፋስ ነው፡፡ "እንደ አውሎ ነፋስ በክፉዎች ላይ እየመጣ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ እስኪሆን የያህዌ ቁጣ አይመለስም

የያህዌ ቁጣ የተነገረው በራሱ ህይወት እንዳለው እና ማድረግ እንደሚችል ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ እስኪሆን የያህዌ ቁጣውን አይመልስም/አያቆምም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልቡ ያለውን ፈቃዱን ይፈጽማል

እዚህ ስፍራ "የልብ ፈቃድ" የሚለው የሚያመለክተው ያህዌ እንዲሆኑ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ነው፡፡ "ያቀደውን ቅጣት ሁሉ ፈጽሞ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የኋልኛው ዘመን

"መጪው ጊዜ"