am_tn/jer/23/16.md

2.7 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤርምያስ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን የያህዌ መልዕክት ማድረሱን ይቀጥላል፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ብዙውን ጊዜ አርምያስ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ ሀሳብን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እነርሱ አሞኝተዋችኋል!

"ነቢያቱ እውነት ያልሆነውን ነገር እንድታምኑ አድርገዋል!"

ከአይምሯቸው የፈለቀውን ቅዠት

እዚህ ስፍራ "አይምሮ" የሚለው የሚያመለክተው የሀሰተኛ ነቢያትን ሀሳብ ነው፡፡ "እነርሱ የሚገምቱት ቅዠት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከያህዌ አፍ ያልሆነ

እዚህ ስፍራ "አፍ" የሚያመለክተው ያህዌ የተናገረውን ነው፡፡ "ያህዌ ያልተናገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ሳያቋርጡ ይናገራሉ

"ሳያቋርጡ" የሚለው ቃል ይህ ሁሌም የሚናገሩት ነገር እንደሆነ አጋኖ በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

በእናንተ ላይ ጥፋት አይመጣም

"በእናንተ ላይ ምንም ክፉ ነገር አይደርስም"

ነገር ግን በያህዌ ምክር ላይ ማን ተገኝቷል?የእርሱን ቃል ማን አይቷል ማንስ ሰምቷል? ለእርሱ ቃል ማን ልቡን ሰጥቶ ሰምቷል?

እነዚህ ጥያቄዎች የዋሉት ካህናቱ እና ሀሰተኛ ነቢያቱ ያህዌን ባለመታዘዛቸው ለመገሰጽ ነው፡፡ "ማንም ያህዌን አላማከረውም፡፡ ማንም ያህዌ የተናገረውን አልተረዳም፡፡ ማንም የያህዌን ትዕዘዞች አልታዘዘም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ ቃላት ትኩረት ስጡ፣ አድምጡም

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ነገር ይገልጻሉ፡፡ በአንድ ሀረግ ሊጠቃላሉ ይችላሉ፡፡ "ሙሉ ለሙሉ ለቃሉን ታዘዙ"