am_tn/jer/22/27.md

1.4 KiB

ሊመለሱባት የሚፈልጉት ይህች ምድር

ይህ የሚያመለክተው የይሁዳን ምድር ነው፡፡

ይህ የተናቀ እና የተሰበረ ዕቃ/ገንቦ ነውን?... አታውቅምን?

በቁጥር 28 ላይ የተናጋሪው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡

ይህ የተናቀ እና የተሰበረ ዕቃ/ገንቦ ነውን? ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው ማንንም ደስ የማያሰኝ ገንቦ ነውን?

ኢኮንያን የተገለጸው አንዳች ጥቅም እንደማይሰጥ ገንቦ እና በማንም እንደማይወደድ ሰው ተደርጎ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ የሚያጎሉት ምንም ዋጋ ወይም ወዳጅ እንደሌለው ነው፡፡ "ኢኮንያን የተሰበረ ዕቃ ያህል ዋጋ የሌለው እና በእርሱ ማንም ደስ የማይሰኝበት ሰው ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

እነርሱን አውጥታችሁ ጣሏቸው

ኢኮንያን እና የእርሱ ትውልዶች የተገለጹት ከእቃ ወጥቶ እንደሚጣል ቆሻሻ ወደ ሌላ አገር እንደተጣሉ ተደርገው ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)