am_tn/jer/22/20.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሰዎች፣ እንደሚጠፉ እየተናገረ ይመስላል፡፡

ድምጻችሁን አንሱ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር መጮህን ያመለክታል፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ በሀዘን እያለቀሱ ነው፡፡ "ጩሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የዓባሪም ተራሮች

በእየሩሳሌም ደቡብ ምስራቅ የሚገኝ የተራራ ሰንሰለት (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላም በነበርክበት ጊዜ ከአንተ ጋር ተነጋግሬያለሁ

"መልካም ታደርግ በነበረበት ጊዜ ከአንተ ጋር ተነጋግሬያለሁ"

ልምድህ ይህ ነበር

"የአኗኗርህ መንገድ እንደዚህ ነበር"

ድምጼን አልሰማህም

መስማት ለመታዘዝ ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ "አንተ እኔን አልታዘዝክም" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)