am_tn/jer/22/13.md

1.4 KiB

ቤቱን የገነባው እርሱ…እንዲህ ይላል

እነዚህ የሚያመለክቱት አዮአቄምን ነው፡፡

ቤቱን በግፍ፣ የላይኛውን ክፍሎች/ሰገነት በፍትህ አልባነት የሰራው

"ግፍ" እና "ፍትህ አልባነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው የተደገሙት ትኩረት ለመስጠት ሲሆን እንደ ድርጊቶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ቤቱን እና የላይኛውን ክፍሎች/ሰገነቱን ለመስራት ሰዎችን በፍትህ አልባነት አስገደደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ቤቱ

"ቤት" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ ንጉሥ ኢዮአቄምን እና ቤተሰቡን ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰገነቱ ላይ ሰፊ ክፍሎች ያሉት ትልቅ ቤት… ሰፋፊ መሰወኮቶች …ጥድ

እነዚህ ባህሪያት ሁሉም በጣም ውድ የሆነን ቤት ይገልጻሉ፡፡