am_tn/jer/22/06.md

2.2 KiB

የይሁዳ ንጉሥ ቤት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ የሚያመለክተው ንጉሡ የሚኖርበትን ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ወይም 2) "ቤት" በቤቱ ለሚኖሩ የይሁዳ ነገሥታት ንጉሳዊ ዝርያ ላላቸው ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "የይሁዳ ንጉሣዊ ስርወ መንግሥት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እንደ ገለዓድ፣ ወይም እንደ ሊባኖስ ከፍተኛ ስፍራ ነህ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "አንተ እንደ ገለዓድ ወይም እንደ ሊባኖስ ጫፍ ውብ ነህ" ወይም 2) "ገለዓድ ወይም የሊባኖስ ጫፍ እንደሚሰጠኝ ያህል ደስታ ትሰጠኛለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ምድረበዳነት እለውጥሃለሁ/ምድረበዳ አደርግሃለሁ

አስቀድሞ ውብ የነበረው ጠፍ እና በረሃ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ "እንደ በረሃ ባዶ ስፍራ እንድትሆን አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አጥፊዎችን በአንተ ላይ አስነሳለሁ

"አንተን እንዲያጠቁ ሰራዊት መርጫለሁ"

ምርጥ የሆኑት ጥዶችህ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የቤተመንግሥቱ አምዶች ወይም 2) የንጉሣዊ ቤተሰብ መሪ የሆኑ ወንዶች፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እሳት ይጣላሉ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የቤተ መንግሥቱን አምዶች የሚያቃጥል እሳት ወይም 2) የንጉሣዊ ቤተሰቦች ጥፋት የተገለጸው በእሳት እንደሚቃጠሉ ተገርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)