am_tn/jer/22/01.md

3.2 KiB

የይሁዳ ንጉሥ ቤት

"የይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት፡፡" "ቤት" የሚለው ቃል የተለያዩ ሰፊ ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው ንጉሡ የሚኖርበትን ንጉሣዊ ቤተመንግስት ነው፡፡

ይህን ቃል ተናገረ/አወጀ

"ይህን መልዕክት አወጀ"

የያህዌን ቃል ስሙ

"ለያህዌ ቃል ትኩረት ስጡ"

በዳዊት ዙፋን የተቀመጥህ አንተ

ይህ የሚያመለክተው የይሁዳን ንጉሥ ነው፡፡

በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጥህ

"ዙፋን" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው ዳዊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ያለን ስልጣን ነው፡፡ "ከአንተ በፊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ዳዊት አስተዳድር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእነዚህ በሮች የሚገቡ የአንተ ሰዎች

እነዚህ በሮች የሚለው የንጉሡ ቤተ መንግስት በሮችን ነው፡፡ "ወደ ንጉሡ የሚመጡ የአንተ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ህትህን እን ጽድቅን አድርጉ

"ፍትህ" እና "ጽድቅ" የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ድርጊቶች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ፍትሃዊ እን ትክክለኛ ድርጊት ፈጽሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም የተዘረፈውን ከጨቋኝ እጅ አድኑት

"የተጠቃውን ከጨቋኞች እጅ አድኑ"

የጨቋኝ እጅ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚገልጸው ሀይልን ወይም መቆጣጠርን ነው፡፡ "የጨቋኙ ሀይል" ወይም "እርሱን ሊጎዳው የሚችል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አትበድሉ

"በክፉ መንገድ አታድርጉ"

የሙት ልጅ

ወላጅ የሌለው ልጅ

ንጹህ ደም… አታፍስሱ

እዚህ ስፍራ "ደም…ማፍሰስ" የተያያዘው ከግድያ ጋር ነው፣ "ደም" የሚያመለክተው የተገደሉ የሰዎችን ነው፡፡ "ንጹሃን ሰዎችን… አትግደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዚህ ስፍራ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እየሩሳሌም ወይም 2) መላው የይሁዳ አገር፡፡ ይህ ሰዎችን በሌላ ስፍራዎች መግደል መልካም ነው የሚል ትርጉም አይሰጥም፡፡