am_tn/jer/21/11.md

2.7 KiB

የይሁዳን ንጉሥ ቤት በሚመለከት፣ የያህዌን ቃል አድምጡ

ይህ ከኤርምያስ 21፡12-23 ድረስ ላለው ክፍል አርእስት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ "ያህዌ ስለ ይሁዳ ንጉሥ፣ ስለ ቤተሰቡ እና ስለ አገልጋዮቹ የሚናገረውን አድምጡ"

የይሁዳ ንጉሥ ቤት

"ቤት" የሚለው ቃል በንጉሡ ቤት ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው ንጉሡን እና ቤተሰቡን ነው፡፡ "የይሁዳ ንጉሥ እና ቤተሰቡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የዳዊት ቤት

ይህ የሚያመለክተው "በይሁዳ ንጉሥ ቤት" እንደሚላቸውን ተመሳሳይ ሰዎች ነው፡፡ መላው የይሁዳ ነገሥታት የዳዊት ትውልድ ናቸው፡፡ "የዳዊት ትውልዶች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በማለዳ ፍትህ ይሆናል

"ፍትህ" የሚለው ረቂቅ ስም ድርጊት ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሁልጊዜም የምትገዟቸውን ሰዎች በትክክል አስተዳድሯቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የጨቋኝ እጅ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው ሀይልን ነው፡፡ "እነርሱን የጨቆነው ሀይል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣዬ እንደ እሳት ወጥቶ ይነዳል

እዚህ ስፍራ የያህዌ ቁጣ የተነገረው ክፉ የሰሩትን እንደሚያቃጥል አሳት ተደርጎ ነው፡፡ "እናንተን በቁጣዬ በቶሎ አንዳችሁንም ሳላስቀር ቀጥቼ አጠፋችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህን ማስቀረት የሚችል የለም

ኤርምያስ በተነጻጻሪ ዘይቤ የቀረበውን የያህዌን ቅጣት በውሃ ሊጠፋ እንደማይችል ታላቅ እሳት መግለጹን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)