am_tn/jer/20/10.md

2.2 KiB

ዘገባ! እኛ ይህን መዘገብ አለብን

የኤርምያስ ጠላቶች እነዚህን ቃሎች ይናገራሉ፡፡

የእኔን መውደቅ ለማየት ይጠባበቃሉ

ኤርምያስ ጠላቶቹ እርሱን ለመክሰስ ስህተት ይሰራል ብለው እንደሚጠባበቁ የሚናገረው ከፍ ካለ ስፍራ ላይ እንደሚወድቅ ሰው አይነት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምናልባት ይታለል ይሆናል… በእርሱ ላይ የበቀል እርምጃ እንወስዳለን

እነዚህን ቃሎች የሚናገሩት የኤርምያስ ጠላቶች ናቸው፡፡

ምናልባት ይታለል ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ምናልባት እኛ ልናታልለው እንችል ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ እንደ ሀያል ጦረኛ ከእኔ ጋር ነው

ኤርምያስ ያህዌ እርሱን መርዳቱን እና ከጠላቶቹ እርሱን ማዳኑን ያነጻጸረው ከታላቅ ጦረኛ ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚያሳድዱኝ ይሰናከላሉ

ኤርምያስ ሊጎዱት የሚፈልጉት ጠላቶቹ እርሱን እንደሚያሳድዱት እና እርሱን ለመጉዳት አለመቻላቸውን ደግሞ እንደተሰናከሉ አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ እጅግ ያፍራሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ በእነርሱ ላይ ታላቅ ሀፍረት ያመጣባቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ፈጽሞ የማይረሳ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች ይህንን ፈጽሞ አይረሱም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)