am_tn/jer/20/07.md

3.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ ወደ ያህዌ ይናገራል

ያህዌ፣ አንተ አታለልከኝ፣ ደግሞም እኔም ተታልዬ ነበር

አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች ይህንን የዕብራይስጥ አገላለጽ "ያህዌ፣ አንተ አሳመንከኝ፣ እኔም ደግሞ አመንኩህ" በማለት ይተረጉሙታል፡፡

እኔ ተታልዬ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ እኔን አታለልከኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኑን በሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤ ሁሉም በእኔ ላይ ያፌዛል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ሌሎች በእርሱ ላይ ያፌዙበትን መንገድ ትኩረት ይሰጣል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መሳለቂያ

ይህ ሌሎች የሚስቁበት እና የሚያፌዙበት ሰው ነው

ተጣራሁ ደግሞም አወጅኩ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ እናም የያህዌን መልዕክት በድፍረት ማወጁን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "በግልጽ አወጅኩ" ወይም "ጮክ ብዩ አወጅኩ/ተናገርኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል በየቀኑ ዘለፋ እና መቀለጃነት አስከተለብኝ

እዚህ ስፍራ "ቃል" የሚያመለክተው የያህዌን መልዕክት ነው፡፡ "ዘለፋ" እና "ፌዝ" የሚሉት ቃላት በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ሰዎች በየቀኑ እኔን ይዘልፋሉ ደግሞም ያፌዙብኛል፤ ይህም የያህዌን መልዕክት ስላወጅኩ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ለእኔ መሳለቂያን ፌዝ ሆነ

"መሳለቂያ" እና "ፌዝ" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ኤርምያስን የያህዌን መልዕክት በማወጁ ሰዎች መሳለቂያ እንዳደረጉት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "ሰዎች በእኔ ላያ የተሳለቁበት ምክንያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ በእርሱ ስም አልናገርም

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በፍጹም ያህዌን አልጠቅስም ወይም ስለ እርሱ ምንም ነገር አልናገርም" ወይም 2) "ስም"የሚለው ቃል ስልጣንን ይወክላል፡፡ "ከእንግዲህ የእርሱ መልዕክተኛ ሆኜ አልናገርም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በልቤ ልክ እንደ እሳት፣ በአጥንቴ ውስጥ እንደሚገኝ ሆነብኝ

እዚህ ስፍራ "ልብ" እና "አጥንት" የሚሉት ቃላት የሚወክሉት የኤርምያስን እጅግ ውስጣዊ ማንነት ነው፡፡ ኤርምያስ የያህዌን መልዕክት አለመናገር እንደማይችል የገለጸው መልዕክቱ በውስጥ እንደሚነድ እሳት መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡ "የያህዌ ቃል በውስጤ እንደሚነድ እሳት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)