am_tn/jer/20/05.md

1.7 KiB

እኔ ለእርሱ እሰጠዋለሁ

እዚህ ስፍራ "እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የባቢሎንን ንጉሥ ነው፡፡

መላው ሀብት… መላው ብልጽግናዋ፣ መላው ውድ ንብረቶቿ እና ጠቅላላ ንብረቷ

ያህዌ መሰረታዊ የሆነውን ተመሳሳይ ሀሳብ አራት ጊዜ የደገመው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ባቢሎን የእስራኤልን ጠቅላላ ሀብት፣ የንጉሡን ንብረቶች ጨምሮ ይወስዳል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህን ነገሮች በጠላቶችህ እጅ ላይ አደርጋለሁ

ነገሮችን በሰዎች እጅ ላይ ማድረግ የሚወክለው ነገሮችን ለሰዎች አሳልፎ መስጠትን ወይም ሰዎች ነገሮችን እንዲወስዱ መፍቀድን ነው፡፡ "እነዚህን ነገሮች ለጠላቶቻችሁ እሰጣለሁ" ወይም "ጠላቶቻችሁ እነዚህ ሀብቶች እንዲወስዱ እፈቅዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እና ሀሰተኛ ትንቢት የተናገርክላቸውን የምትወዳቸውን በሙሉ በዚያ ይቀበራሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በዚያ፣ ሰዎች አንተን እና የምትወዳቸውን ሀሰተኛ ነገሮችን የተናገርክላቸውን ሁላችሁምን ይቀብሯችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)