am_tn/jer/20/03.md

2.1 KiB

እንዲህ ሆነ

ይህ ሀረግ እዚህ ስፍራ የዋለው ድርጊቱ የት ላይ እንደ ጀመረ ለማመልከት ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህ የሚገልጽበት መንገድ አዚህ ስፍራ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

አንተ ማጎር ሚሳቢብ ነህ

የዚህ ስም ትርጉም "በሁሉም በኩል ሽብር" ወይም "በሽብር መከበብ" ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እዩ፣

ይህ ቃል ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት ይጨምራል፡፡ "ቀጥሎ ለምናገረው ትኩረት ስጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እነርሱ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ

"በሰይፍ መውደቅ" የሚለው ፈሊጥ ትርጉም በጦርነት ይሞታሉ ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጠላቶቻቸው በሰይፍ ይገድሏቸዋል" ወይም "ጠላቶቻቸው በጦርነት ውስጥ ይገድሏቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ዐይኖችህ ይህንን ይመለከታሉ

እዚህ ስፍራ "ዐይኖች" የሚለው ቃል የሚወክለው ጳስኮርን ነው፡፡ "አንተ ይህን ትመለከታለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

መላዋን ይሁዳ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል ሀይልን ያመለክታል፡፡ "የባቢሎን ንጉሥ መላውን ይሁዳ እንዲማርክ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)