am_tn/jer/20/01.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ ትንቢት የሚጽፈው በሥነ ግጥም መልክ ነው፡፡ የዕብራውያን ስነግጥም የተለያዩ የትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ አይነቶችን ይጠቀማል፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጳስኮር… ኢሜር

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ጳስኮር ኤርምያስን መታው

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ጳስኮር ራሱ ኤርምያስን መታው ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም 2) ጳስኮር ሌሎች ሰዎች ኤርምያስን እንዲመቱት አዘዘ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማሰሪያ/እግር ግንድ

ማሰሪያ ግንድ፣ ከእንጨት የተሰራ በመሃሉ ቀዳዳያለው ሰዎች የእስረኞችን እጆች፣ እግር፣ እና ጭንቅላት ለማሰሪያ/ለመጠረቅ የሚጠቀሙበት ግንድ ነው፡፡

የላይኛው የብንያም በር

ይህ በር በከተማይቱ ቅጥር መግቢያ ከሚገኘው ተመሳሳይ ስም ካለው በር ይለያል