am_tn/jer/19/04.md

1.3 KiB

እነርሱ እኔን ትተዋል

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳን ሰዎች ነው፡፡

ይህንን ስፍራ በንጹሃን ደም ሞልተውታል

እዚህ ላይ "የንጹሀን ደም" የሚለው የሚወክለው የንጹሃን ሰዎችን መገደል ነው፡፡ ያህዌ የብዙ ሰዎችን መገደል አንድን ስፍራ በደም መሙላት አድርጎ ይናገራል፡፡ "በዚህ ስፍራ ብዙ ንጹሃን ሰዎችን ገድላችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ይህ ወደ አይምሮዬ አልገባም/አላሰብኩትም

እዚህ ስፍራ "አይምሮ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የያህዌን ሃሰብ/ፈቃድ ነው፡፡ በኤርምያስ 7፡31 ላይ ይህ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እኔ በፍጹም ስለዚህ አስቤ አላውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)