am_tn/jer/15/13.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ቁጥሮች፣ ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል፡፡

ሀብት እና ንብረት

"ሀብት" እና "ንብረት" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የሚያመለክቱትም ሰዎች ሰዎች ዋጋ አላቸው ብለው የሚቆጥሯቸውን ነገሮች ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ዝርፊያ

አንድን ከተማ ከወረሩ በኋላ በሃይል የተወሰዱ/የተሰረቁ ነገሮች

የፈጸምካቸው ኃጢአቶች በሙሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የፈጸምካቸው በደሎች በሙሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በድንበሮችሁ ውስጥ ሁሉ

"በመላው አገርህ"

የማታውቀው ምድር

"ለአንተ ባዕድ በሆነ ምድር"

እሳት ይቀጣጠላል፣ በአንተ ላይ ቁጣዬ ይነዳል

እዚህ ስፍራ ያህዌ ቁጣውን እሳት እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ቁጣዬ በአንተ ላይ እንደማነደው እሳት ነው" ወይም "በቁጣዬ እመጣብሃለሁ፣ ደግሞም ቁጣዬ እንደሚነድ እሳት ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማንደድ/ማቀጣጠል

እሳት መለኮስ