am_tn/jer/15/10.md

3.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ቁጥሮች ኤርምያስ ስለ መከራው ወደ ያህዌ ይጮሃል/ይናገራል ያህዌም ይመልስለታል፡፡

አወይ ለእኔ፣ ምነው እናቴ

ኤርምያስ እንዴት እንዳዘነ ለማጉላት የሚገልጽበት መንገድ ለእናቱ የሚናገር ይመስላል፡፡ (አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

አነጋጋሪ እና የክርክር ሰው

"አነጋጋሪ" እና "አከራካሪ" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በአንድነት ኤርምያስ ምን ያህል እንደሚከራከር ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "የሰው ሁሉ መነጋገሪያ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ለማንም አላበደርኩም፣ ወይም ማንም አላበደረኝም

ይህ የሚያመለክተው ለሰዎች ገንዘብ ማበደርን ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ማበደር ሰዎች እርስ በእርሳቸው እንዲጋጩ ያደርጋል፡፡ "እኔ ለማንም ገንዘብ አላበደርኩም፣ አሊያም ማንም ለእኔ ገንዘብ አላበደረኝም" ወይም "ከብድር የተነሳ ማንንም አላስቆጣሁም ወይም ገንዘብ ተበድሬ ከዚያ የተነሳ ከማንም ጋር አልተጣላሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለመልካም አልታደግህምን?

ለዚህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በውስጠ ታዋቂነት የሚሰጠው ምላሽ "አዎን" የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በእርግጥ ለመልካም እታደግሃለሁ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ጠላቶች

ከትንቢቱ ጋር የማይስማሙት እነዚያ የኤርምያስ ጠላቶች ናቸው

በመከራ እና በጭንቀት ጊዜ

እዚህ ስፍራ "መከራ/መቅሰፍት" እና "ጭንቀት/ስቃይ" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በአንድነት ሆነው የስቃዩን መጣን ያጎላሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ብረትን የሚያደቅ አለን? በተለይም ከነሐስ ጋር የተደባለቀን የሰሜን ብረት መስበር የሚችል ሰው አለን?

በእነዚህ ጥያቄዎች ያህዌ፣ የይሁዳ ጠላቶችን ጥንካሬ ከነሐስ ጋር እንደ ተደባለቀ ብረት አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ብረትን መስበር አይችልም፣ በተለይም ከነሐስ ጋር እንደ ተደባለቀው የሰሜን ብረት ያለውን ማንም አይሰብረውም፡፡" ወይም "ነገር ግን እንደ ብረት ወይም ነሀስ ጠንካራ ሆኑት ጠላቶቹ ይሁዳን ከሰሜን ያጠቁታል፣ ደግሞም ማንም ሊያስቆማቸው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)