am_tn/jer/14/17.md

2.0 KiB

ቀንና ሌሊት

እዚህ ላይ ሁልጊዜ ለማለት የቀኑ ሁለት ተቃራኒ ጊዜያቶች ተሰጥተዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ፣ ቀንና ሌሊት በሙሉ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሕዝቤ ድንግል ሴት ልጅ

እዚህ ላይ እግዚብሔር የእርሱ ሕዝብ ለእርሱ ብርቅየና የተወደደ እንደሆነ ሲናገር እነርሱ የእርሱ ድንግል ሴት ልጅ እንደሆኑ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ድንግል ሴት ልጅ የምሳሳላቸው ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይፈወስ ቁስል

ሊፈወስ የማይችል በቆዳ ላይ የሚከሰት መቆረጥ ወይም ስብራት

በሰይፍ የሞቱ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ በተጨማሪ “ሰይፍ” እዚህ ላይ ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሰይፍ የሞቱ ሰዎች” ወይም “በጦርነት የሞቱ ሰዎች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በረሃብ ምክንያት የመጡ በሽታዎች አሉ

እዚህ ላይ “በሽታዎች” የሚለው በረሃብ ከመሰቃየታቸው የተነሳ እነዚህ በሽታዎች ያሉባቸውን ሰዎች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎች አሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ይቅበዘበዛሉ

ያለ ዓላማ ወዲህና ወዲያ መንቀሳቀስ

አያውቁም

እነርሱ ምን እንደማያውቁ መግለጹ ሊጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምን እንደሚሰሩ አያውቁም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)