am_tn/jer/14/15.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስ ሐሰተኛ ነቢያቶች ስለሚተነብዩት ነገሮች ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነበር፡፡

በስሜ

ይህ ሀረግ በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን ወይም እንደ እርሱ ወኪል መናገርን ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 14:14 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም ሰይፍ አይኖርም … ሰይፍ አይኖርም

እዚህ ላይ “ሰይፍ” ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም ጦርነት አይኖርም … ጦርነት አይኖርም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያን ጊዜ ትንቢት የተነገረላቸውም ሕዝብ ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ይበተናሉ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ማለት የቤተሰብ አባላት በሙሉ ይሞታሉ፣ ሕዝቡም አስከሬኖቻቸውን ከመቅበር ይልቅ በመንገዶቹ ላይ ይጥላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በዚያን ጊዜ ትንቢት የተነገረላቸው ሕዝብ በራብና በሰይፍ ይሞታሉ፣ ሕዝቡም አስከሬኖቻቸውን በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ይጥሉአቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን

ይህ የሚያብራራው “እነርሱ” በሚለው ቃል የተመለከቱትን ሰዎች ነው፣ ይህም በራብና በሰይፍ የሞቱትን ሰዎች በሙሉ ማለት ነው፡፡

እኔ ክፋታቸውን በእነርሱ ላይ አፈስስባቸዋለሁ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ክፋታቸው መጠን እንደሚቀጣቸው ሲናገር የሕዝቡ ክፋት ፈሳሽ እንደሆነና እርሱ ይህን ፈሳሽ በእነርሱ ላይ እንደሚያፈስስባቸው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሊቀጡ እንደሚገባቸው እኔ እቀጣቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)