am_tn/jer/14/13.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ለኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ እንዳይጸልይላቸው ነገረው፡፡

ሰይፍ አታዩም

እዚህ ላይ “ሰይፍ” ጦርነትን ይወክላል፣ “ማየት” ደግሞ በሁኔታው ውስጥ ማለፍን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአንድም ጦርነት ውስጥ አታልፉም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እውነተኛ ደህንነት እሰጣችኋለሁ

እዚህ ላይ “ደህንነት” አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሊሰጠው የሚችለው እቃ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በደህንነት እድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ” ወይም “እኔ በሰላም እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የውሸት ትንቢት ይናገራሉ

“ውሸት” የሚለው ቃል እንደ ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመዋሸት ይተነብያሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በስሜ

ይህ ሀረግ በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን ወይም እንደ እርሱ ወኪል መናገርን ያመለክታል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ እነርሱን አልላክኋቸውም

ይህ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲያስተላልፉ መልእክት ሰጥቶ አልላካቸውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለሌሎች ሰዎች ትንቢት እንዲናገሩ አልላክኋቸውም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከራሳቸው አእምሮ የሚወጣ

እዚህ ላይ “አእምሮ” ሃሳብን የማሰብ ችሎታ ሳይሆን የሆነ ስፍራ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ራሳቸው ያሰቡትን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)