am_tn/jer/14/10.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ብቻቸውን እንዳይተዋቸው ይጸልያል ደግሞም እግዚአብሔርን ይጠይቃል፡፡

መቅበዝበዝን ይወድዳሉ

“ከእኔ ርቀው ሄደው መቅበዝበዝን ይወድዳሉ፡፡” ይህ የሚናገረው ለእግዚአብሔር ታማኞች ስላልሆኑ እርሱን ስለማይታዘዙት ሕዝብ ነው፣ ሕዝቡን እርሱ ከሚኖርበት ቦታ ርቀው በመሄድ እንደተቅበዘበዙ አድርጎ ገልጦአቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግራቸውንም አልከለከሉም

እዚህ ላይ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ርቀው መሄዳቸውን አጽንዖት ለመስጠት “እግሮቻቸው” በሚለው ቃል ተገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳቸውን አልጠበቁም” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያስባል

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያስታውሳል” ወይም “አይረሳም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ፤ በ … ስም

“መደገፍ” ወይም “መርዳት”

ማልቀስ

በሃዘን ምክንያት በታላቅ ጩኸት ማልቀስ

ለእነርሱ ፍጻሜ አበጅላቸዋለሁ

ይህ ለስላሴ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እንዲሞቱ አደርጋቸዋለሁ” (ለስላሴ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ

እዚህ ላይ ጦርነት “በሰይፍ” ተወክሏል፣ ሰይፍ በውጊያ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል የተለመደ መሳሪያ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጦርነት” ወይም “በውጊያ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)