am_tn/jer/14/07.md

3.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ በኩል ለሕዝቡ ስለ ድርቅ ተናግሯቸዋል፡፡

ኃጢአታችን በእኛ ላይ ይመሰክርብናል

እዚህ ላይ “ኃጢአቶች” ስለ ክፉ ስራቸው በእነርሱ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጠአታችን ለክፉ ስራችን ማስረጃ ይሰጣሉ” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ ስምህ ብለህ

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ስም” መልካም ማንነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ መልካም ማንነትህ ብለህ” ወይም “ማንኛውም ሰው አንተ በጣም ታላቅና ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ እንደሆንህ ማየት ይችል ዘንድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ተስፋ

ይህ የእግዚአብሔር ሌላ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በምድር እንደ እንግዳ ለምን ትሆናለህ … ግራ እንደተጋባ ሰው ለምን ትሆናለህ

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለቱም ጥያቄዎች እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ግድ የማይሰኝ እንደሆነና እነርሱን ለመርዳት የማይችል እንደሆነ ይጠይቃሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በምድር እንደ እንግዳ ለምን ትሆናለህ፣ እንደ ባዕድ መንገደኛ … አንድ ሌሊት ብቻ

ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመርዳት ቸልተኛ የሆነበት ሁኔታ እንዳለ ሲናገር እርሱ በዚያ ስፍራ ስለሚኖሩ ሰዎች ግድ የሌለው በዚያ መንገድ የሚያልፍ እንግዳ መንገደኛ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያ የሚያልፍና አንድ ሌሊት ብቻ የሚያድር ሰው

ሁለቱም ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ስለዚህ በአንድ ላይ ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንድ ሌሊት ብቻ የሚቆይ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ግራ እንደተጋባ ሰው፣ ወይም ያድን ዘንድ እንደማይችል ተዋጊ ስለ ምን ትሆናለህ?

ይህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመርዳት ያልቻለበት ሁኔታ እንዳለ ሲናገር እርሱ ማንንም ሰው ማዳን ያልቻለ ግራ የተጋባ ተዋጊ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ግራ መጋባት

አንድን ነገር ለመረዳት ወይም በግልጽ ለማሰብ አለመቻል

ስምህ በእኛ ላይ ተጠርቷል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ስሙ በእነርሱ ላይ እንደተጠራ በመናገር ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስምህን ተሸክመናል” ወይም “እኛ የአንተ ሕዝብ ነን” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ and ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)