am_tn/jer/14/04.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ በኩል ስለ ድርቅ ለሕዝቡ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች እፍረታቸውን ለማሳየት ራሳቸውን የሚሸፍኑበት ልብስ ይለብሱ ነበር፡፡ (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ ተወች፣ ግልገሎቿን ተወቻቸው

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የሚበላ ነገር ባለመኖሩና ልትሰጣቸው ስላልቻለች የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ እንደ ተወች አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ ተወች” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ሳር የለምና

ለአጋዘን የሚሆን የሚበላ ሳር የለም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእነርሱ የሚሆን የሚበላ ሳር የለምና” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ቀበሮም በነፋስ ውስጥ አለከለኩ

ይህ እንደ ቀበሮ አለከለኩ በማለት አህዮች ማለክለካቸው ይናገራል ምክንያቱ ደግሞ ጥም ስለበረታባቸው ነው፡፡ ቀበሮ ብዙ የሚያለከልኩ በጣም አደገኛ የሆኑ የዱር ውሻዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ተጠማ ቀበሮ በነፋስ ውስጥ ያለከልካሉ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አትክልት የለምና ዓይኖቻቸው ፈዘዙ

“የሚበሉት ሳር ስለሌለ ታወሩ”