am_tn/jer/13/25.md

2.0 KiB

እኔ ለአንቺ የሰጠሁሽ፣ ለአንቺ ያወጅኩልሽ ድርሻሽ ይህ ነው

እነዚህ ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በይሁዳ ሕዝብ ላይ እግዚአብሔር እንዲሆንባቸው የወሰነው እነዚህ ነገሮች እንደሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእናንተ ላይ እንዲሆን ያደረግሁት ነገር ይህ ነው” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ራሴ የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል

ይህ እግዚአብሔር እፍረት እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህን ሲል በየትኛውም መንገድ ይደፍራቸዋል ማለት አይደለም፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንኛውም ሰው እፍረትሽን እንዲያይና እፍረት እንዲሰማሽ ለማድረግ እኔ ራሴ የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እንደሚገልጥ እሆናለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ማሽካካት

ይህ ወንድ ፈረስ ሴት ፈረስን ሲፈልግ የሚሰማው ድምጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መመኘት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)