am_tn/jer/13/22.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ለይሁዳ ንጉስና ለንጉሱ እናት ምን እንደሚላቸው ለኤርምያስ እየነገረው ነው፡፡

የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል

ይህ የጠላት ጦር ሰራዊት አባላት የይሁዳን ሴቶች ይደፍሯቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጠላት ጦር ሰራዊት አባላት የሴቶቻችሁን ቀሚስ እየገለቡ ይደፍሯቸዋል፡፡ (ለስላሴ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በውኑ የኩሽ ሕዝብ የቆዳውን ቀለም ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው የአንድ የማይቻልን ነገር ምሳሌ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ በተጨማሪ “ይችላል” የሚለው ግልጽ ግስ በሁለተኛው ሀረግ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኩሽ ሕዝብ የቆዳውን ቀለም ሊለውጥ አይችልም፣ ነብር ደግሞ ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ አይችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ ከሆነ ምንም እንኳ ክፋትን የለመዳችሁ ብትሆኑም እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ

ይህ ዓረፍተ ሃሳብ ምጸታዊ ነው ምክንያቱም ስለ ኩሽ ሕዝብና ስለ ነብር የተሰጠው ምሳሌ የማይቻሉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የማይቻሉ ነገሮች የተቻሉ ከሆነ እነርሱም መልካም ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ነገሮች የማይቻሉ እንደሆኑ እንደዚሁ ሁልጊዜ ክፋትን ማድረግ ለለመዳችሁ ለእናንተ መልካምን ማድረግ አይቻላችሁም” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

የምድረ በዳ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ እንዲሁ እበታትናችኋለሁ

“በነፋስ እንደሚበታተን ገለባ እንዲሁ እበታትናችኋለሁ፡፡” ገለባ በነፋስ እንደሚበታተን እንደዚሁ እግዚአብሔር ሕዝቡን በዓለም ዙርያ እንደሚበታትናቸው እየተናገረ ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)