am_tn/jer/13/15.md

1.9 KiB

ትዕቢት

አንድ ሰው ከእውነታው ውጭ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ስለራሱ ማሰብ

እርሱ ጨለማ ያመጣል

“እርሱ ጨለማ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡” እዚህ ላይ ችግርና ተስፋ መቁረጥ “ጨለማ” እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ጨለማና ተስፋ መቁረጥ ያመጣል” ወይም “ትልቅ መከራ እንዲመጣ ያደርጋል”

እርሱ እግራችሁ እንዲሰናከል ከማድረጉ በፊት

እዚህ ላይ ሰው እየተራመደ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት “በእግሩ” ተገልጾአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንድትራመድና ስትራመድ ተሰናክለህ እንድትወድቅ ከማድረጉ በፊት” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን ድንግዝግዝ ሲል

ማለዳ ወይም ምሽት በከፊል ጨለማ ሲሆን፣ ጸሐይ መውጣት ስትጀምር ወይም ጸሐይ መግባት ስትጀምር

ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፣ ነገር ግን እርሱ ስፍራውን ወደ ድቅድቅ ጨለማ ይለውጠዋል፤ ድቅድቅ ደመናም ያደርገዋል

ይህ መልካምነትንና በረከትን እንደ “ብርሃን” መከራና ተስፋ መቁረጥን ደግሞ እንደ “ጨለማ” ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ብርሃንና በረከት ተስፋ ታደርጋላችሁ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ጨለማንና ታላቅ ተስፋ መቁረጥ ይሰጣችኋል፣ በድቅድቅ ደመናም እንደተከበባችሁ ይሰማችኋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና

x