am_tn/jer/13/12.md

3.2 KiB

ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንኛውም የወይን አቁማዳ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማንኛውም የወይን አቁማዳ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” ወይም “ማንኛውም የወይን ማሰሮ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማንኛውም የወይን ማሰሮ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከቱ

ይህ ቃል እዚህ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዳምጡ” ወይም “ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”

በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ

“የዚህችን ምድር ነዋሪዎች በሙሉ እንዲሰክሩ አደርጋቸዋለሁ”

በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት

እዚህ ላይ የይሁዳ ንጉስ የሚቀመጥበት ዙፋን “የዳዊት ዙፋን” በሚለው ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ዙፋን የሚቀመጡ ነገስታት” ወይም “የይሁዳ መንግስት ነገስታት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱን ሰው ከሌላው ሰው ጋር፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣለሁ

እዚህ ላይ “እያንዳንዱ ሰው” የሚሉት ቃላቶች ወንዶችንና ሴቶችን በሙሉ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያም እኔ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ አደርጋቸዋለሁ፣ ወላጆችና ልጆች ሳይቀር እርስ በርሳቸው ይጣላሉ” (የተባዕት ቃላት ሴቶችንም ሲያካትት የሚለውን ይመልከቱ)

አባቶችና ልጆች በአንድ ላይ

ግልጽ የሆነው መረጃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ እቀጠቅጣቸዋለሁ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

አላዝንላቸውም

“ሃዘን ፈጽሞ አይሰማኝም”

ከጥፋት አላድናቸውም

“ቅጣቱን ከእነርሱ አልመልስም፡፡” ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲጠፉ እፈቅዳለሁ”