am_tn/jer/13/08.md

3.3 KiB

የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል መጣ” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ የሚጠቅም ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 1:4 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከትና እንደ አስፈላጊነቱ ማንኛውንም ለውጥ አድርግ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ፡-“ ወይም “እግዚአብሔር ይህን ሁለተኛውን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡-“ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳና የእስራኤል

እዚህ ላይ የይሁዳና የኢየሩሳሌም የሚለው የሚያመለክተው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሌን ለመስማት

“እኔ የተናገርሁትን ለመታዘዝ”

በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም እልከኞች የሆኑና ምኞታቸውን ብቻ የሚያደርጉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደምትጣበቅ … ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ

“እንደሚለጠፍ … ከእኔ ጋር ተለጥፈዋል” ወይም “ተጠግተው እንደሚቆዩ … ከእኔ ጋር ተጠግተው ቆይተዋል”

ቤት ሁሉ … ቤት ሁሉ

“ሕዝብ ሁሉ … ሕዝብ ሁሉ”

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ እዚህ ላይ የእስራኤልን መንግስት ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤል” ወይም “የእስራኤል መንግስት” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ እዚህ ላይ የይሁዳንና የቢንያምን ልጆች የሚያካትተውን የይሁዳን መንግስት ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይሁዳ” ወይም “የይሁዳ መንግስት” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)