am_tn/jer/13/01.md

1.4 KiB

የተልባ እግር

በጣም ቀጭንና ስስ የሆነ ልብስ

መታጠቂያ

ሰዎች ከልብሳቸው በታች የሚለብሱት፣ የውስጥ ልብስ

ወገብ

ብዙ ጊዜ ቀጭንና ጠባብ የሆነው በዳሌና በደረት መካከል ያለው የሰው አካል መካከለኛው ክፍል

በመጀመርያ በውኃ ውስጥ አትንከረው

“አትጠበው ወይም እርጥበት አታስነካው

ለሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል መጣ” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ከእግዚብሔር ዘንድ የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ የሚጠቅም ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 1:4 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከትና እንደ አስፈላጊነቱ ማንኛውንም ለውጥ አድርግ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ፡-“ ወይም “እግዚአብሔር ይህን ሁለተኛውን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡-“ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የዓለት ንቃቃት

በውስጡ አንድ ነገር ለማስቀመጥ የሚበቃ በአለት መካከል ያለ ክፍት ቦታ ወይም በአለት ላይ ያለ ስንጥቅ