am_tn/jer/12/14.md

1.6 KiB

ርስታቸውን ለመንጠቅ

“ምድሪቱን ለመውሰድ እየሞከሩ ነው”

ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት

“ለሕዝቤ ለእስራኤል እንደ ርስት የሰጠሁትን”

ተመልከቱ

ይህ ቃል እዚህ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዳምጡ” ወይም “ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”

እነርሱን ከምድራቸው ለመንቀል

እግዚብሔር ሕዝቡ ምድራቸውን እንዲለቅቁ ስለማስገደዱ ሲናገር እነርሱ ከምድር እንደሚነቅላቸው ተክሎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ ይህንን ሃሳብ በኤርምያስ 1:10 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የራሳቸውን ምድር እንዲለቅቁ ለማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ የሎሎችን ሕዝቦች ምድር እንዲለቅቁ እንደሚያደርጋቸው ሲናገር ከምድር እንደሚነቅላቸው ተክሎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የይሁዳን ቤት ምድራቸውን እንዲለቅቁ አደርጋቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነቅለዋለሁ

x