am_tn/jer/12/12.md

2.1 KiB

አጥፊው መጥቷል

“የሚያጠፋ ጦር ሰራዊት መጥቷል”

በምድረ በዳ ባሉት ወና ኮረብቶች

“ምንም ነገር በማይበቅልባቸው በምድረ በዳ ያሉ ስፍራዎች”

የእግዚአብሔር ሰይፍ ይበላልና

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመቅጣት ስለሚጠቀምባቸው ጦር ሰራዊቶች ሲናገር እነርሱ የእርሱ “ሰይፍ” እንደሆኑ አድርጎ ገልጾታል፡፡ እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ሰይፍ” ሕዝቡን የሚያጠቃና የሚበላ በጣም ትልቅ እንስሳ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጦአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “”ጦር ሰራዊቶች እናንተን ለመቅጣት የምጠቀምባቸው የእኔ ሰይፍ ናቸው” ወይም “እናንተን እንዲያጠቁ የሚያጠፋ ጦር ሰራተዊት ልኬባችኋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ

ይህ የሚያመለክተው የሕዝቡ ርስት የሆነውን መሬት በሙሉ ነው፡፡

እነርሱ ስንዴን ዘሩ ነገር ግን እሾህን አጨዱ

“እነርሱ ስንዴን ዘሩ ነገር ግን እሾህን አጨዱ እንጂ ሌላ ነገር ምንም አልሰበሰቡም”

እነርሱ

“የእኔ ሕዝብ”

የእሾህ ጥሻ

ዙርያው በእሾህ የተሞላ ትልቅ ተክል

ደከሙ

የበለጠ ለመስራት አለመቻል፣ አቅምና ጉልበት ማጣት

ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሳ ምንም ስላላገኛችሁ ታፍራላችሁ

“ስለዚህ እግዚአብሔር እናንተን ስለተቆጣ የሰበሰባችሁት በጣም ትንሽ ስለሆነ ታፍራላችሁ፡፡” እዚህ ላይ “የሰበሰባችሁት” የሚለው ቃል ትልቅ መጠን ያለው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የሚያመለክተው እጅግ በጣም ትንሽ ነገር ነው፡፡