am_tn/jer/12/10.md

1.5 KiB

ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተውታል

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ምድሩና ሕዝቡ በጠላቶች ስለ መጥፋታቸው ሲናገር ሕዝቡ እረኛው እንዳጠፋው እንደ ወይን ቦታ አድርጎ ገልጦአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቤና ምድሬ ብዙ እረኞች እንዳጠፉት የወይን ቦታ ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ እረኞች አጥፍተውታል

እዚህ ላይ “እረኞች” የሚለው ቃል በጎቻቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ እረኞች በጎቻቸው እንዲያጠፉት ፈቅደውላቸዋል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉንም ረጋግጠውታል

“በእግራቸው ረጋግጠውታል”

እድል ፈንታዬ የሆነው ምድር

“እኔ የተከልሁት ቦታ” ወይም “የእኔ እርሻ”

ምድሪቱ ባድማ ሆናለች

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በልቡ የሚያስባት

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚንከባከባት” ወይም “ትኩረት የሚሰጣት” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)