am_tn/jer/12/07.md

4.8 KiB

ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጆች አሳልፌ ሰጥቻለሁ።

እነዚህ ሶስት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አንደኛውና ሁለተኛው ዓረፍተ ነገሮች የሶስተኛውን ሃሳብ ያጠናክራሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር “ቤቱ” እና “ርስቱ” እንደሆኑ አድርጎ የገለጸበት ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእኔ እንዲሆኑ የመረጥኋቸውን የእኔ የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ ትቻቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጠላቶችዋ እጆች

እዚህ ላይ “እጆች” የሚለው በቁጥጥር ስር ማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጠላቶቿ ለመሸነፍ” ወይም “በጠላቶቿ ቁጥጥር ስር እንድትሆን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሷ … እርሷ ተነሳችብኝ … ከእርሷ ጋር … እርሷን ጠላኋት

እዚህ ላይ ሕዝቡን የአንስታይ ጾታ ተውላጠ ስም በመጠቀም እግዚአብሔር ሕዘቡን እንደ ሴት ይጠራዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱ … እነርሱ … ራሳቸውን አዘጋጁ … ከእነርሱ ጋር … እነርሱን ጠላኋቸው” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷ በራሷ ድምጽ በእኔ ላይ ተነሳችብኝ

ይህ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንደ አንበሳ አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ይህ ሕዝቡ በእግዚብሔር ላይ እንደሚያገሱ አድርጎ በመግለጽ እነርሱ በእግዚብሔር ላይ እንደተነሱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔን ለመቃወም በእኔ ላይ እንደምታገሳ ሆናለች”

የተወደደች ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን?

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በጠላቶቻቸው እንደተከበቡ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተወደደች ርስቴ በዙርያዋ ሁሉ እንደተከበበች እንደ ዝንጉርጉር አሞራና ሌሎች የሚታደኑ ወፎች ሆናለች፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የተወደደች ርስቴ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር የእርሱ “የተወደዱ ርስት” እነደሆኑ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ሕዝብ፣ የተወደዱ ሕዝቤ … አይደሉምን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን?

እዚህ ላይ እግዚአብሔር በአደጋ ላይ ስላለውና በጠላቶቹ ስለተከበበው ስለ ሕዝቡ ሲናገር በአዳኝ ወፎች እንደተከበበ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሷ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ ሆነች፣ ጠላቶቿም ደግሞ በሁሉም አቅጣጫ እርሷን እንደሚያጠቁ እንደ አዳኝ ወፎች ሆነዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝንጕርጕር አሞራ

“ያልተለመደ መልክ ያለው እንግዳ ወፍ፡፡” ይህ ብዙ ጊዜ በሌሎች ወፎች የሚታደንና የሚበላ ወፍን ያመለክታል፡፡

አደን የሚድኑ አሞሮች

እንስሳትን የሚያጠቁና የሚበሉ ወፎች

ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሏትም ዘንድ አምጡአቸው

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር ለማጠናከር በትዕዛዝ መልክ ይናገራል፡፡ ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው ለተወሰነ ግለሰብ አይደለም ስለዚህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሜዳ ያሉ የምድር አራዊት ሁሉ ይምጡና ይብሏት” (እንቶኔ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)