am_tn/jer/12/05.md

2.2 KiB

ከፈረሰኞች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የሚያመለክተው እርሱ ከፈረሶች ጋር ሊሮጥ እንደማይችል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ከፈረሶች ጋር ፈጽሞ ልትወዳደር አትችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )

ብትወድቅ

ይህ ሰው እየሮጠ ቢወድቅ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እየሮጥህ እያለህ ብትወድቅ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰላም ምድር

ይህ በፍጥነት ለመጓዝ ቀላል የሆነውን የተመቻቸ ሜዳ የሚያመለክት ሲሆን ለመንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት በዮርዳኖስ ወንዝ ዙርያ ካሉት የቁጥቋጦ ጥሻዎች ጋር እያነጻጸረ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በዮርዳኖስ ዙርያ ባሉት የቁጥቋጦ ጥሻዎች መካከል በእርግጠኝነት መሮጥ አትችልም”

በዮርዳኖስ ወንዝ ዙርያ ባሉት የቁጥቋጦ ጥሻዎች እንዴት ታደርጋለህ?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የሚያመለክተው በዮርዳኖስ ወንዝ ዙርያ ባሉት የቁጥቋጦ ጥሻዎች መካከል ሊሮጥ እንደማይችል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በዮርዳኖስ ወንዝ ዙርያ ባሉት የቁጥቋጦ ጥሻዎች መካከል ልትሮጥ በእርግጥ አትችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የቁጥቋጦ ጥሻዎች

ብዙ ቁጥቋጦ ወይም ትንንሽ ዛፎች በአንድነት ተጠጋግተው የበቀሉበት

ተወግዘሃል

አንድን ሰው በአደባባይ በሕዝብ ፊት መወንጀል