am_tn/jer/12/03.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስ ለእግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ልቤ

እዚህ ላይ “ልብ” የሰውን ሃሳብና እውነተኛ ስሜት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ሃሳቦች” ወይም “የእኔ የውስጥ ስሜት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ዕርድ ቦታ እንደሚወሰዱ በጎች ውሰዳቸው

እዚህ ላይ ኤርምያስ ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት እንዲዘጋጅ እግዚብሔርን ሲጠይቅ እነርሱ ለመታረድ እንደሚወሰዱ በጎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎችን ለመታረድ እንደሚነዱ በጎች ውሰዳቸው” ወይም “ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት ተዘጋጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የዕርድ ቀን

“እነርሱ የሚጠፉበት ቀን”

በእርሷ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳ ምድሪቱ የምትደርቀው እስከ መቼ ነው?

በሰዎች ክፋት ምክንያት ቅጣት ስለተላለፈባቸው ምድራቸው ደርቃለች፣ ዝናብ ደግሞ አይዘንብም፡፡

መጠውለግ

መድረቅ

እንስሳቱና ወፎቹ ተወስደዋል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንስሳቱና ወፎቹ ሄደዋል” ወይም “እንስሳቱና ወፎቹ በሙሉ ሞተዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚሆነውን ነገር አያይም

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሕዝቡ በወደፊት ሕይወታቸው በእነርሱ ላይ ምን ነገሮች እንደሚፈጸሙ እግዚአብሔር አያውቅም እያሉ ይናገራሉ ወይም 2) እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን አያውቅም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እኛ የምንሰራቸውን ኃጢአት የተሞሉ ነገሮችን አያይም”