am_tn/jer/11/18.md

3.5 KiB

እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንዳውቃቸው አደረገኝ፣ እኔም አወቅኋቸው

“አንተ ነገሮችን ለእኔ ገለጥህልኝ፣ እኔም አወቅኋቸው፡፡” ይህ ጠላቶቹ እርሱን ለመግደል እያቀዱ እንደነበረ እግዚአብሔር ለኤርምያስ መግለጡን የሚያመለክት ነው፡፡

ስራቸውን እንድመለከት አደረግኸኝ

ይህ ጠላቶቹ እርሱን ለመግደል እያቀዱ እንደነበረ እግዚአብሔር ለኤርምያስ መግለጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እዚህ ላይ የተነገረው ኤርምያስ የእነርሱን ስራዎች እንደተመለከተ አድርጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱን ክፉ እቅዶች ለእኔ ገለጠልኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ

ይህ ኤርምያስን ለመታረድ ከሚነዳ ከየዋህ በግ ጋር በማነጻጸር ኤርምያስ እርሱን ለመግደል ጠላቶቹ ያቀዱትን እቅድ አለማወቁን ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለመታረድ ወደ እርድ ቦታ እንደሚነዳ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቼ ወደ እርድ ቦታ እየመሩኝ ነው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ

እዚህ ላይ የኤርምያስ ጠላቶች እርሱን ለመግደል ስለማሰባቸው ሲናገር ኤርምያስ እነርሱ ሊያጠፉት ያቀዱት የፍሬ ዛፍ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ከሕያዋን ምድር እናጥፋው

“እናጥፋው” የሚለው ቃል እርሱን ማጥፋት ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ “ሕያዋን” የሚለው ሕያዋን ሕዝብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእነዚህ በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ምድር ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይኖር እንግደለው” ወይም “በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ዓለም መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይኖር እናጥፋው” ( ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ከእንግዲህ ወዲህ ስሙን አያስታውሱትም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብንና አእምሮን

“ልብ” የሚለው ሰው ለሚሰማው ስሜትና ለሚፈልገው ነገር ምትክ ስም ነው፣ “አእምሮ” ደግሞ ሰው ለሚያስበውና ለሚወስነው ነገር ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰው ስሜትና ሃሳብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በቀልህን እኔ እመሰክራለሁ

እዚህ ላይ “በቀል” የሚለው ቃል በግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ስትበቀል እኔ እመለከትሃለሁ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)