am_tn/jer/11/14.md

2.6 KiB

ስለ እነርሱ ልትማጠን አይገባህም

“ታላቅ የሃዘን ልቅሶ ልታለቅስ አይገባህም”

ወዳጄ፣ እጅግ በጣም ብዙ ክፉ ሃሳብ የነበራት በቤቴ ውስጥ ምን አላት?

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመበት የይሁዳ ሕዝብ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለወደፊት ለመገኘት ምንም ዓይነት መብት እንደሌለው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ወዳጄ፣ እጅግ በጣም ብዙ የክፋት ሃሳብ የነበራት፣ በቤቴ ውስጥ ልትገኝ አይገባትም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህች ወዳጄ፣ የነበራት

የይሁዳ ሕዝብ እጅግ እንደተወደደች እንደ አንዲት ሴት ተደርጋ ተነግራለች፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የምወዳቸው ሕዝቤ፣ የነበራቸው” ወይም “እኔ የምወዳቸው የይሁዳ ሕዝብ፣ የነበራቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ባለፉት ዘመናት እግዚአብሔር የለመለመ የወይራ ዛፍ ብሎ ጠርቶሽ ነበር

በብሉይ ኪዳን ሰዎች ብዙ ጊዜ ከዛፎችና ከተክሎች ጋር ይነጻጸሩ ነበር፡፡ ፍሬያማና ጤናማ የነበሩት የለመለሙና ጤናማ ዛፎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባለፉት ዘመናት እግዚአብሔር እናተ እንደለመለመ የወይራ ዛፍ እንደነበራችሁ ተናግሯል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሷ ላይ እሳት ያነድድባታል

ይህ ገለጻ የዛፉን ተለዋጭ ዘይቤ ተከትሎ የተነገረ ነው፡፡ እሳቱ የሚወክለው የሕዝቡን መጥፋት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህም የታላቅ ዓውሎ ነፋስ ድምጽ ይኖረዋል

ይህ የአስከፊውን እሳት ድምጽ ከኃይለኛ ዓውሎ ነፋስ ድምጽ ጋር ያኘጻጽረዋል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅርንጫፎቹ ይሰባበራሉ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅርንጫፎችሽን ይሰባብራቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)