am_tn/jer/11/06.md

1.7 KiB

የተከበረ

ትኩረት የሚሰጠውና በጣም ጠቃሚ

የዚህን ቃል ኪዳን ቃል

“የዚህ ቃል ኪዳን ውሎች”

አድርጉት

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ታዘዙአቸው” (የሚለውን ይመልከቱ)

ድምጼን ስሙ

እዚህ ላይ “ድምጽ” የሚለው ቃል ተናጋሪው በድምጹ ለተናገረው ነገር ምትክ ስም ነው፣ “ስሙ” የሚለው ደግሞ “ለመታዘዝ” ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተናገርሁትን ታዘዙ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልቡ እልከኝነት ይመላለስ ነበር

እዚህ ላይ “መመላለስ” የሚለው አንድ ሰው ለሚኖርበት የኑር ዘይቤ ፈሊጥ ነው፡፡ “ልብ” የሚለው ደግሞ ለሰው ፍላጎትና ስሜት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ሰው ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆነም፣ ይልቁንም በራሱ ክፉ ፍላጎት ይኖር ነበር” ወይም “እያንዳንዱ ሰው ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆነም፣ ይልቁንም ማድረግ የሚፈልጉትን ክፉ ነገሮች ማድረግ ቀጠሉ” (ፈሊጥ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ በእነርሱ እንዲመጡ ያዘዝኋቸውን በዚህ ቃል ኪዳን ያሉትን እርግማን ሁሉ አመጣሁባቸው

“ስለዚህ እነርሱ እንዲታዘዙት በነገርኋቸው በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ ባሉት እርግማኖች ሁሉ ቀጣኋቸው”