am_tn/jer/11/03.md

1.3 KiB

ማንኛውም ሰው የተረገመ ነው

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ማንኛውንም ሰው እረግማለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ከግብጽ አገር ከብረት ማቅለጫው ምድጃ

ይህን የሚናገረው እስራኤላውያንን ከብረት ማቅለጫ ምድጃ ጋር በማነጻጸር እስራኤላውያን ይኖሩ የነበረውን አስከፊ ሁኔታና ጭቆና ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የግብጽ፡፡ በግብጽ ምድር በእነርሱ የሆነው እጅግ በጣም አስከፊ ነበር፤ ይህ ሁኔታቸው አነርሱ በጣም በጋለ ምድጃ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ያህል ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማቅለጥ

ብረትን ወደ ፈሳሽ ለመለወጥ ማቅለጥ

ድምጼን አድምጡ

“ድምጽ” የሚለው ተናጋሪው በድምጹ ለተናገረው ነገር ምትክ ስም ነው፣ “አድምጡ” የሚለው ደግሞ “ለመታዘዝ” ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምናገረውን ታዘዙ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)