am_tn/jer/09/25.md

3.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ የእግዚአብሔር ቃላት ናቸው፡፡

ተመልከቱ

እግዚአብሔር እዚህ ላይ ይህን ቃል የተጠቀመው ከዚህ ክፍል ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድምጡ” ወይም “በእርግጥ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀናት እየመጡ ነው

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጊዜ ይኖራል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋቸውን ብቻ የተገረዙትን

ይህ በስጋቸው በመገረዝ ወደ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የገቡትን ነገር ግን የእርሱን ሕግ በመከተል ውስጣዊ ማንነታቸውን ያልለወጡ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውጫዊ ሰውነታቸውን በመገረዝ የለወጡ ነገር ግን ውስጣዊ ማንነታቸውን ያልለወጡ ሕዝብ በሙሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በራሳቸው ላይ ያለውን ጸጉር በአጭሩ የሚቆረጡ ሕዝቦች በሙሉ

ይህ ምናልባት የሚያመለክተው የአሕዛብ ጣዖት ለማክበር ሲሉ ጸጉራቸውን በአጭሩ የሚቆረጡ ሕዝቦችን ነው፡፡ አንዳንድ አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን የዕብራይስጥ አገላለጽ “በምድረ በዳ ጫፍ ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች በሙሉ” ብለው ተርጉመውታል፡፡

እነዚህ ሕዝቦች የተገረዙ አይደሉምና

እዚህ ላይ “ሕዝቦች” የሚለው ቃል በእነዚህ ስፍራዎች የሚኖሩትን ሕዝቦች ነው፡፡ ያልተገረዙ እንግዳ ሰዎች በእግዚአብሔር ኪዳን ውስጥ ያልተካተቱ ለመሆናቸው ምልክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነዚህ መንግስታት ሕዝቦች በመገረዝ ወደ እግዚአብሔር ኪዳን አልገቡም” (ምትክ ስም እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት በሙሉ ያልተገረዘ ልብ አላቸው

“ልብ” የሰውን ፈቃድና ፍላጎት ይወክላል፡፡ “ያልተገረዘ ልብ” እግዚአብሔርንና ሕጉን የማይከተል ሰው ባህርይ ይወክላል፡፡ ከዚህ በተጨማሩ የእስራኤል “ቤት” የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ የተገረዙት በውጫዊው ሰውነታቸው ብቻ ነው፣ ልባቸው ግን አልተለወጠም” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)