am_tn/jer/09/19.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚናገረው እርሱ ምድሪቱን ሲያጠፋ ወደፊት የይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን ነው፡፡

በጽዮን የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል

ይህ የጽዮን ሕዝብ ከፍ ባለ ድምጽ ማልቀሱን የሚያመለክት ሲሆን በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጽዮን ሕዝብ ከፍ ባለ ድምጽ ያለቅሳሉ፣ እንዲህ እያሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ እንዴት ፈራረስን

ምድሪቱ በምትጠፋበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ወደፊት የሚናገረውን እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ በጣም ተበሳጭተናል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቶቻችንን ስላፈረሱና ምድሪቱን ስለተውን እኛ እጅግ በጣም አፍረናል

“እፍረታችን እጅግ ታላቅ ነው፣ ምክንያቱም ጠላቶች ቤቶቻችንን አፍርሰውታል የእስራኤልን ምድር ደግሞ ለቅቀን መውጣት አለብን”

የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ከአፉ ለሚመጣው መልእክት ተገቢ ትኩረት ስጡ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲያደምጡ ለሰጠው ትእዛዝ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ በሁለተኛው ሀረግ የእግዚብሔ “አፍ” ለራሱ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረውን አድምጡ፡፡ ለቃሉ ትኩረት ስጡ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ የጎረቤት ሴቶች የቀብር ልቅሶውን

ግልጽ የሆነ ግስ መጠቀም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእያንዳንዱ የጎረቤት ሴቶች የቀብር ልቅሶውን አስተምሩአቸው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)