am_tn/jer/09/17.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ለሚመጣው ለምድሪቱ ጥፋት እንዲያለቅሱ ይነግራቸዋል፡፡

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

ኤርምያስ ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም አስፈላጊ መልእክት ለማስተዋወቅ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት ይጠቀማል፡፡ ይህን በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

የቀብር አልቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ … የሰለጠኑ ሙሾ አውራጆችን አስመጡ፤ ይምጡ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እነዚህ ሀረጎች የቀብር አልቃሾች እንዲያመጡ ሊጠሩአቸው እንደሚገባ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰለጠኑ አልቃሽ ሴቶች ፈልጋችሁ አግኙና እነዚህን ሴቶች ወደዚህ አምጡአቸው” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

የቀብር አልቃሾችን ጥሩ

“በቀብር ላይ ሙሾ የሚያወጡ የሰለጠኑ አልቃሽ ሴቶች ጥሩ”

ይምጡ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲመጡ ለሴቶቹ ንገሯቸው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰለጠኑ ሙሾ አውራጅ ሴቶችን ለመፈለግ ሰው ላኩ

“ሰው ላኩ” የሚለው ሀረግ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ “የልቅሶ ሙሾ በማውረድ የሰለጠኑ ሴቶችን ለማግኘት ሰዎችን ላኩ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የእኛ የዓይናችን ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ

x