am_tn/jer/09/13.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ምክንያቱም

“እነዚህ ነገሮች ይሆናሉ ምክንያቱም”

ሕጌን ትተዋልና

እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሕጉን አለመታዘዝ ሲናገር ከሕጉ ርቀው እንደሄዱ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕጌን ትተውታል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድምጼን አይሰሙም

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ድምጽ” እርሱ የተናገረውን ነገር ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለእነርሱ ለነገርኋቸው ነገሮች ምንም ትኩረት አልሰጡም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም በእርሱ አልሄዱም

እዚህ ላይ “መሄድ” ፈሊጥ ሲሆን “መኖርን” የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወይም እኔ እንዲኖሩ በነገርኋቸው መንገድ አልኖሩም” ( ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በልባቸው እልከኝነት ሄዱ

እዚህ ላይ የሕዝቡ “እልከኛ ልቦች” እልከኛ ፍላጎታቸውንና እልከኛ ፈቃዳቸውን ይወክላል፡፡ እዚህ ላይ “መሄድ” መኖርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እልከኞች ነበሩና ሊኖሩ በሚፈልጉት መንገድ ኖሩ” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በኣሊምን ተከተሉ

“በኣልን አመለኩ”