am_tn/jer/09/10.md

4.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ በቁጥር 12 ኤርምያስ አስተያየት ይሰጣል፡፡

እኔ የሃዘን ልቅሶ አለቅሳለሁ … ለማሰማርያዎቹ የቀብር ልቅሶ ይለቀሳል

የሞተች ሰው እንደሆነች በማሰብ እንደዚሁ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር ያለቅሳል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀብር ልቅሶ ይለቀሳል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የቀብር ልቅሶ አለቅሳለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ማሰማሪያዎቹ

“እንስሳት ሳር የሚግጡበት የግጦሽ ስፍራ”

እነርሱ ተቃጥለዋልና

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምክንያቱም ሰው ማሰማሪያዎቹንና የግጦሽ መሬቱን አቃጥሎአቸዋልና” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንድም ከብት ድምጽ ፈጽመው አይሰሙም

“በዚያ ስፍራ አንድም ሰው የከብት ድምጽ አይሰማም”

የቀበሮ መሸሸጊያ

“ቀበሮዎች የሚደበቁበት ስፍራ፡፡” ቀበሮዎች እጅግ በጣም ኃይለኛ የዱር ውሾች ናቸው፡፡

ሰው የማይኖርበት ስፍራ

“አንድም ሰው የማይገኝበት ስፍራ”

ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው?

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ የተናገራቸውን ነገሮች መረዳት የሚችል ሰው በጣም ጥበበኛ ሰው ብቻ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ነገሮች መረዳት የሚችሉ በጣም ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው እነዚህን ነገሮች መናገር የሚችሉት እርሱ የተናገራቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ነገሮች ለሌሎች ማብራራት የሚችሉት ከእግዚአብሔር የተማሩ ብቻ ናቸው” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር አፍ

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ንግግር በእርሱ “አፍ” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው እንዳያልፍባት ምድሪቱ ለምን ጠፋች፣ ለምንስ ወና ሆነች?

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው ምድሪቱ ለምን እንደጠፋች ማብራራት የሚችለው ጥበበኛ ሰው ብቻ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው እንዳያልፍባት ምድሪቱ ለምን እንደጠፋች እና ወና እንደሆነች ማብራራት የሚችለው ጥበበኛ ሰው ብቻ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )

ምድሪቱ ጠፍታለች ደግሞም ወና ሆናለች

ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ “ጠፋች” እና “ወና ሆነች” የሚሉት ሁለቱም ምድሪቱ ወና እንደሆነች የሚያብራሩ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ ወና ሆናለች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)