am_tn/jer/09/07.md

4.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ተመልከት

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ይህን ቃል የተጠቀመው የኤርምያስን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚናገረው ንግግር ለመሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድምጥ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን ለማንጠር

እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለመፈተንና ክፉ መንገዳቸውን ፊት ለፊት ስለመጋፈጥ ሲናገር እነርሱ ብረት እንደሆኑና እርሱ የብረቱን ቆሻሻ ለማስወገድ ብረቱን በማቅለጫ እንደሚያቀልጠው አድርጎ ገልጾታል፡፡ ( ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሕዝቤ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ምን ማድረግ እችላለሁ?

እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው ከሰሩት ስራ የተነሳ ሕዝቡን ሊጋፈጥ የሚያስፈልገው በዚህ መንገድ እንደሆነ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዐረፍተ ሃሳብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሰሩት ስራ የተነሳ ከሕዝቤ ጋር መጋፈጥ የሚገባኝ እንደዚህ ነው” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ምላሶቻቸው የተሳሉ ቀስቶች ናቸው

ይህን የሚናገረው ሰዎች በሚናገሩት ንግግር ሌሎች ሰዎችን በጣም ሲለሚጎዱ የሰዎች ምላሶቻቸው የተሳሉ ቀስቶች እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ እዚህ ላይ ንግግራቸው “በምላሶቻቸው” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቃላቶቻቸው ሌሎች ሰዎችን እንደሚጎዱ እንደተሳሉ ቀስቶች ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በአንደበቶቻቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ሰላምን ይናገራሉ

እዚህ ላይ የሰዎች ንግግር “በአንደበቶቻቸው” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከባልንጀሮቻቸው ጋር ሰላም እንፈልጋለን እያሉ ይናገራሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን በልባቸው አድብተው ይጠብቁአቸዋል

እዚህ ላይ የሰዎች ፍላጎት “በልባቸው” ተወክሏል፡፡ አደን ወጥቶ ለመብላት የሚፈልገውን ለማጥቃት እንደሚያደፍጥና እንደሚጠብቅ እንስሳ እንደዚሁ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን ለመጉዳት የሚፈልጉ እንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እነርሱ የሚፈልጉት ነገር ባልንጀሮቻቸውን ማጥፋት ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ስለነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን? … እኔ ራሴስ እንደዚህ ዓይነቱን ሕዝብ አልበቀልምን?

እግዚአብሔር እነዚህን መልስ የማይሰጥባቸውን ጥያቄዎች የተጠቀመው እነርሱ የሰሯቸው ነገሮች በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳ በእነርሱ ላይ ምህረት እንደማይኖረውና እነርሱን ከመቅጣት ራሱን እንደማያስቆም አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ እነዚህን ተመሳሳይ ቃላት በኤርምያስ 5፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እነዚህን ነገሮች ከማድረጋቸው የተነሳ እኔ እቀጣቸዋለሁ … እኔ ራሴ በእርግጠኝነት በእነርሱ ላይ እበቀላለሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)