am_tn/jer/09/04.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ከኤርምያስ ጋር መነጋሩን ቀጥሏል፡፡

እናንተ እያንዳንዳችሁ

“እናንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡

ከጎረቤቶቻችሁ ተጠብቀቁ፣ በወንድሙም ላይ አይታመን

“አብረዋችሁ ያሉትን እስራኤላውያንን ከማመን ተጠንቀቁ፣ የራሳችሁን ወንድም ቢሆንም አትመኑ”

እያንዳንዱ ጎረቤት በሐሜት ይመላለሳል

እዚህ ላይ “ይመላለሳል” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን መኖርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ጎረቤት አንዱ ሌላውን ያማል” ወይም “እያንዳንዱ ጎረቤት ሐሜተኛ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ሰው በጎረቤቱ ላይ ያፌዛል፣ እውነትን ደግሞ አይናገርም

“ሁሉም ሰዎች እርስ በርሳቸው ያፌዛሉ፣ እውነትን ደግሞ አይናገሩም”

ምላሶቻቸው ሐሰተኛ ነገሮችን ያስተምራሉ

እዚህ ላይ ለንግግራቸው አጽንዖት ለመስጠት ሲባል ሰዎች “በምላሶቻቸው” ተወክለዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሐሰተኛ ነገሮችን ያስተምራሉ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉንም በማድረግ ደክመዋል

“ብዙ ኃጢአት በማድረግ ደክመዋል”

መኖርያችሁ በሽንገላ መካከል ነው

እግዚአብሔር በውሸታሞች መካከል መኖር በሽንገላ መካከል መኖር እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መኖርያችሁ በውሸታሞች መኖርያ መካል ነው” ወይም “እናንተ የምትኖሩት በውሸታሞች መካከል ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሽንገላቸው

“እነዚህን ሁሉ ውሸቶች በመናገር”

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)